Annual Shareholders Meeting

  • Home
  • Annual Shareholders Meeting

Arifpay Financial Technologies S.C Conducted its Shareholders Meeting Successfully.

አሪፍፔይ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂስ አ.ማ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤዉን በተሳካ ሁኔታ አካሄዷል::

የአሪፍፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ አ.ማ. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ነው። በዚህም
መሰረት የአሪፍፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በእለተ
እሑድ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም (January 15, 2023) በአዲስ አበባ በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል።
የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤው የተካሄደውም በአካል እና በኤሌክትሮኒክስ (Online) ሲሆን ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ
ዉሳኔዎችን አስተላልፏል።
ይህ ጉባኤም ማህበሩ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ካገኘ በኋላ የተለያዩ የዝግጅት ስራዎችን ከሰራ በኋላ በNovember 2022
ከቤሔራዊ ባንክ የመጀመሪያዉን የCommercialization Letter ባገኘበተ እና ማህበሩ በ December 15, 2022
በተካሄውደው ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ማግስት መደረጉ የዘንድሮውን የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ልዩ
እንደሚያደርገው የተገለፀበት ነበር።
እንድሁም ጉባኤው ያስተላለፋቸው ዉሳኔውች ማህበሩ በሚቀጥለው የስራ ዓመት የበለጠ ዉጤታማ ሆኖ በእትዮጵያ
የፋይናንስ ዘርፍ ዉስጥ ምሳሌያዊ ሚናዉን እንዲወጣ የሚረዳ መሆኑ እሙን ነው።
አሪፍፔይ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂስ አ.ማ ይህ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን አስታዉፆ ላደረጋቹ ለዳይሪከተሮች ቦርድ፣ በሁሉም
ደረጃ ላሉ ለማህበሩ የማነጅመንት አባላት በጉባኤው ለተገኛቹ እንግዶች እና ከሁሉም በላይ ለማህበሩ ባለአክስዪኖቻችን ላቅ
ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።

ከአሪፍፔይ ጋር ሁሉም አሪፍ ነው።
ጥር 2015 ዓ.ም
January 2023